“ህይወቱን ለሰጠኝ ደሜን እሰጠዋለሁ ” በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 5 – 15/2015 ድረስ የሚቆይ የደም ማሰባሰቢያ መርሀግብር በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ
“ደማችን ለጀግናው የሀገር ለመከላከያ ሰራዊታችን“ ሀገራዊ ጥሪን መነሻ ያደረገ የደም ልገሳ መከናወኑን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የጤናው ሴክተር የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ክንውን ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ውይይት ጉባኤ ሂደት ደማችን ለጀግናው የሀገር የሰብሃዊነት ተግባር የሆነው የደም ልገሳ አገልግሎት ከፍ ለማድረግና የደም አቅርቦት ፍላጎትን ለማሳካት በፈቃደኛነት ላይ የተመሰረተ የደም ልገሳ ሚናው የጎላ ነው፡፡ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው በበጎ ፈቃደኝት ደም እየለገሱ ለሚገኙ እንደሁም በተለያዩ ግዜያቶች በቋሚነት ደም በመለገስ ለወገን ደራሽነታቸውን ላሳዩ ሁሉ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ ምስጋናቸውን አቅርበው በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ደም መለገስ የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በለጋሾቹም ሰብአዊነት በሚገለጽበትና የአህምሮ እርካታን በሚያጎናፅፈው የደም ልገሳ ተግባር በመሳተፋቸው ደስታን እንደፈጠረላቸው በለጋሹ ጤና ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳያመጣ ለሌላው ህይወት አድን መሆኑ ይበልጥ ደም እንዲለግሱ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ