ኮሮና ቫይረስ በገንዘብ እና በማይዝጉ ቁሶች ላይ ለ28 ቀን ሳይሞት እንደሚቆይና በሽታ ሊያስተላልፍ ይችላል

ኮሮና ቫይረስ በገንዘብ እና በማይዝጉ ቁሶች ላይ ለ28 ቀን ሳይሞት እንደሚቆይና በሽታ ሊያስተላልፍ እንደሚችል በአውስትራሊያ የተደረገ ጥናት አመለከተ።
ኮሮና ቫይረስ ከተገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ በቁሶች ላይ እንደሚቆይ ያረጋገጠው የአውስትራሊያ ብሄራዊ ሳይንስ ኤጀንሲ በጥናት መለያው ሳርስ ኮቭ 2 በተሰኘው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ይህ አዲሱ የተመራማሪዎች ግኝት ቫይረሱ ከቁሶች ወደ ሰዎች የሚተላለፍበት መጠንም ከተገመተው በላይ ፈጣን ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ተማራማሪዎች አልትራ ቫዮሌት (ዩቪ) ብርሃን ቫይረሱን ሊገድለው እንደሚችልም መግለጻቸው ይታወሳል።
ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ምርምሮች ኮሮና ቫይረስ በገንዘብ ኖቶች እና ጠርሙሶች ላይ ከሁለት እስከ ሶስት ቀናት እንዲሁም በፕላስቲክ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ደግሞ እስከ ስድስት ቀናት ሊቆይ እንደሚችል ገልጸዋል።
አውስትራሊያውያኑ ባካሄዱት ምርምር ግን ብርሀን በሌለበት እና 20 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሙቀት ባለው ክፍል ውስጥ ቫይረሱ በጠርሙሶች እና በስልክ ስክሪኖች ላይ እስከ 28 ቀናት ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።
ተመራማራች አክለውም በጥናቱ እንደተመለከተው፤ኮሮናቫይረስ ሞቃታማ በሆነ ክፍል ውስጥ ለረዥም ጊዜ አይቆይም።
በሌላ በኩል ጉንፋን የሚያስከትሉ ቫይረሶች በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ከተቀመጡ እስከ 17 ቀናት ድረስ ሊቆዩ ይችላሉ።
ቫይረሱ በጨርቅ ላይ ከ14 ቀናት በላይ እንደማይኖርም በጥናት ውጤቱ ላይ ተጠቁሟል።
የተመራማሪዎቹ ጥናት ሰዎች እጆቻቸውን እና የስልክ ስክሪኖቻቸውን በተደጋጋሚ ማጽዳት እንዳለባቸው የሚያስታውስ መሆኑ ነው የተገለፀው መሆኑን ምንጭ ቢቢሲን አድርጎ ኢቢሲ ዘግቦታል፡፡