ህብረተሰቡን ያሳተፈ ዳግም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት መከላከልና መቆጣጠር ተግባራትን ማጠናከር መቆጣጠር የጥንቃቄ እርምጃዎች መተግበርና ማስተግበር እንደሚገባ የሁልባረግ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የህብረተሰቡን ዋና ዋና የጤና ችግሮችን በመፍታት ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት የኮቪድ _19 ወረርሽኝ ለመግታት የተከናወኑ ተግባራት በውጤታማነታቸው ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ ዳግም እተቀሰቀሰ ያለው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ ክስተት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በህብረሰቡ ጤና ላይ ተጽዕኖ ማሳረፉ አልቀረም፡፡
የሁልባረግ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አብዱ አማን ሰሞኑን በተከሰተው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ ክስተት በአከባቢው መታየቱ ይህም የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ስርጭት በፍጥነት እንዲጨምር ማድረጉን አውስተው መዘናጋትና መሰላቸት በመቅረፍ ስርጭቱን ለመግታትና ሐማስቆም የህብረተሰቡ ትብብርና ጥረት ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ሚና እንደ አዲስ ለማነቃቃት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የሁልባረግ ወረዳ ነዋሪዎቹ ወ/ሮ ሽቱ ጉረሰቦ እንዲሁም ወ/ሮ ዘያዳ ከማል የፈጣሪ እገዛ ታክሎ በኮቪድ ሳቢያ የሚከሰተው ህመምና ሞት መቀነሱ እፎይታን የፈጠረ ቢሆንም ዳግም በአከባቢው ህፃናትን ጭምር የሚያጠቃው በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው ጉንፋን ብዙዎች ዘንድ የጤና መታወክን እየፈጠረ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎቻቸውን ጭምር በተገቢው እንዳያከናውኑ ተግዳሮትን እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡
በቀጣይነት የህዝብ መሰባሰብ በጉልዕ በሚስተዋልባቸው በሀይማኖት ተቋማት ፣በገበያ ስፍራዎች ፣ በትራንስፖርት በትምህርት እና በሌሎች አገልግሎት መስጫ አከባቢዎች የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም ህብረተሰቡን ዳግም በማነቃነቅ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት መከላከልና መቆጣጠር ተግባር ትኩረት ይሠጠው ብለዋል::