ሁሉም ማህበረሰብ ስለ ጤና መረጃ እንደ አስፈላጊነቱ የመጠየቅና የማግኘት መብት አለዉ

“የጤና መረጃን ማዛባት የጤና፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ስለሚያስከትል ልንፀየፈው ይገባል” በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘው የጤና ሳምንት በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በማክበር የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው የጋራ ርብርብአካል ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
የህብረተሰቡን ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዘመነ የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናከር ሚናው የላቀ በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ ስለ ጤና መረጃ እንደአስፈላጊነቱ የመጠየቅና የማግኘት መብት አለዉ በሚል በህለቱ መርሕ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በተለያዩ አከባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
በዚህ ረድ የጤና መረጃ ጥራቱን ለማስጠበቅና ተአማኒነቱን ለማረጋገጥ በየጊዜዉ የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የማዘመን ስራ ጤና ተቋማት ደረጃ ተግባራዊ የተደረገ በትክክለኛ በጤናዉ ሴክተር የዘመነ የጤና መረጃ ስርዓትን ማጠናከር መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት በእጅጉ ያግዛል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ