ehost expert review with uptime

ማህበረሰቡን በማነቃነቅና ተሳትፎውን ከፍ በማድረግ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ስርጭት መከላከልና መቆጣጠር ይገባል ፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ ዘርፈ ብዙ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምላሽን፣ የምክርና ምርመራ እና የድጋፍና ህክምና አገልግሎቶችን በተመለከተ ሶስት የውይይት መነሻ ፅሁፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀደም የነበረው የተጠናከረ ርብርብ በመቀነሱና መዘናጋት በመከሰቱ ስርጭቱን መግታት ያልተቻለ ችግር ለመሻገር በተጠናከረ ርብርብ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የክልሉ አመራሮች፣ የዞንና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የጤና መምሪያ ኃላፊዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ በክልል ደረጃ በፓናል ውይይት የተጀመረው የዓለም ኤድስ ቀን በነገው ዕለትም በተለያዩ የንቅናቄ ዝግጅቶች ታስቦ እንደሚውል ከወጣው የድርጊት መርሀ-ግብር ለመረዳት ተችሏል፡፡ የአለም ኤድስ ቀን "ማህበረሰብ የለውጥ አቅም ነው "በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተጀመረ ። የክልል:የዞንና የልዩ ወረዳ አመራሮች እና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጧፍ ማብራት ፕሮግራም ተጠናቋል።