ehost expert review with uptime

የሚገኝባቸዉ ወገኖች ማህበራትና ጉዳዩ ያሳሰባቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት፡- ሻይረሱ በደማቸዉ የሚገኝባቸው ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያሻቅብ ምክንያት በሚሆኑ አባባሽ ሁኔታዎች ላይ በርብርብ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ፤ በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ የሚስተዋሉ የአደንዛዥ እፆች ንግድ ላይ የህግ ተጠያቂነትን መሰረት ያደረገ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት 0.4 በመቶ ነዉ ቢባልም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በከተሞች ያለዉ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ጌታሁን ጋረደዉ ይህም ወደ ወረርሽኝነት እየተለወጠ ሊሄድ የሚችል አስጊ ሁኔታ ላይ መሆናችንን የሚያሳይ መሆኑን በመረዳት መላዉን የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረገ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ላይ አመራሩ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በዚሁ ዕለት በተለይም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ለችግሩ የሚሰጠው ትኩረት እየቀነሰ መምጣቱ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና የተለያዩ ማህበራትን አሳትፎ በመስራት ረገድ ክፍተት መኖሩ፣ቫይረሱ ይገኝባቸዋል ተብሎ የሚገመቱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ያደረጉ እንቅስቃሴዎች አመርቂ አለመሆናቸዉ እና ቫይረሱ ለሚገኝባቸዉ ወገኖች የሚደረገዉ ድጋፍና እንክብካቤ ያነሰ መሆን ለስርጭቱ መስፋፋት እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ በመጨረሻም የዉይይቱ ታዳሚዎች ቃለ መሃላ በመፈፀም ስርጭቱን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡